loading
ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም ድጋፍ ጠየቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ጠየቀች፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ብለው የጠሩት የእሳት አደጋ በአስር ሺዎች ሄክታር የሚለካ መሬት መሸፈኑ ተነግሯል፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ሳርዲኒያ በተባለች ደሴት ሲሆን በርካታ የደሴቷ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከአደጋው ለማዳን መኖሪያ አካባቢዎቻቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡

ፈረንሳይና ግሪክ የጣሊያን መንግስት ያቀረበውን የድጋፍ ጥሪ ተቀብለው የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ወደስፍራው መላካቸውን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ከ7 ሺህ 500 በላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች በቦታው ተሰማርተው እሳቱን ለማጥፋትና የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የሞት ሪፖርት አልተሰማም ፡፡

የአሶሼትድ ፕሬስ ደግሞ የእሳት አደጋው በ100 ሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋሪ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል፡፡ አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የሙቀት መጠኑ ተጠናክሮ እደሚቀጥልና ይህም የአደጋውን መጠን ሊያባብሰው እንደሚችል የሀገሪቱ የአየር ትንበያ ተቋም አስጠንቅቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *