ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እየሰጡ ነዉ፡፡
የምክር ቤት አባላቱ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸዉ 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልታጠቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸዉን እና የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ መሆኑን ከፓርቲዎች ጋር የተደረጉ ድርድሮችም በሰላም መርህ መሰረት የተከናወኑ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሀገር ዉስጥ የገቡት ፓርቲዎች የተሻለ ሀሳብ አምጥተዉ ሀገሪቱን ከድህነት የሚያወጣ፤ ሰላሟን የሚያረጋግጥ ሀሳብ ማፍለቅ አለባቸዉ ብለዋል ።
የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለድርድር አይቀርብም፤ መንግስት በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ዙሪያ ከማንም ጋር አይደራደርም፤ ህግንም ተመስርተን እርምጃ እንወስዳለብለዋል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡት የተፎካሪ ፓርቲዎች አብዛኛዎቹ ዴሞክራሲ በሀገሪቱ እንዲሰፍን እየሰሩ ነው ሆኖም ከገቡት መካከል ጉራማይሌ የሆነ ባህሪ ያላቸው አሉ፤ ይህ ጉራማይሌ አካሄድ መቆም ይገባዋል፡፡
ችግር እየፈጠሩ ተጠቃሚ ለመሆን የሚጥሩ አካላት አሉ፤በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ምህዳሩ ሰፍቷል በዚህም የረጅም ርቀት ለመሮጥ ትንፋሽ የሚያጥራቸው ፓርቲዎች አሉ።
አሁን የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ አንድነቷን፣ ሰላሟን እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሀሳብ ያለው ፓርቲ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ አንድነት የሚገዳደር ሀይል ካለ በኢትዮጵያ ጦርነት አውጇል ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡