ጠ/ሚር አብይ አሕመድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የ100 ቀናት ዕቅድን የአፈፃፀም ግምገማ እየመሩ ነዉ።
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የ100 ቀናት ዕቅድን የአፈፃፀም ግምገማ እየመሩ ነዉ።
ከእነዚህ ግምገማዎች በተጨማሪ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹና ተጠሪ ተቋማት እንደገና ለሚቀጥሉት የ 100 ቀናት ዕቅዶች በማውጣት በሂደት እንዲተገበሩ ይጠበቃል።
ይህ የዕቅድ እና አፈፃፀም ግምገማ ሂደት ተቋማዊ ተጠያቂነትና የሥራ አፈፃፀምን ለማረጋገጥ የተዘረጋ አሰራር ነው ተብሏል።
በዘሬው እለት የአፈጻጸም እቅዳቸውን የሚያቀርቡት የፋይናንስ፣ የሰላም፣ የንግድና ኢንዱስትሪና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ናቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፖሊሲና አፈጻጸም ክፍል አባላት ወሳኝና የሚኒስትር መስሪያ ቤቶቹ ን ተቋማዊ አፈጻጸም እንዲያጠናክሩ የሚያስችሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
የሌሎች መስሪያ ቤቶች ግምገማና ውይይት እስከ ነገ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።