loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የጋምቤላ ክልል ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ አስገነዘቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የጋምቤላ ክልል ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ አስገነዘቡ

አርትስ 16/02/2011
 የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ የማዕከላዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ እያካሄደ ባለው  ግምገማ
 የፓርቲው ሊቀመንበር እና የክልሉ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑነት አቶ ጋትሉዋክ ቱት እና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ከኃላፊነታቸው ለቀው አቶ ኦሙድ ኡጁሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አኙአያ ጃከን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር መሆናቸው ትናንት ተነግሯል፡፡
በግምገማው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የክልሉ ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር ጊዜውን በግል አጀንዳዎችና ሽኩቻ ከማጥፋ ይልቅ ራሱን ከጎሰኝነትና ከጥላቻ በማጽዳት የክልሉን አመራር በማጠናከር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል፡፡
ክልሉ በርካታ ሙያተኞች በየዩኒቨርሲቲው፣ በፌዴራል፣ በክልሉም ሆነ በዳያስፖራ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን በማፈላለግ በየደረጃው ክልሉን ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል ብለዋል፡፡
ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮችም በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸው እና ህዝቡን ለመካስ በተመደቡበት የስራ መስክ ለመሰማራት መወሰናቸው መልካም መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *