loading
ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር አብይ አሕመድ ከፕራይቬታይዜሽን አማካሪ ምክር ቤት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር አብይ አሕመድ ከፕራይቬታይዜሽን አማካሪ ምክር ቤት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከፕራይቬታይዜሽን አማካሪ ምክር ቤት ጋር የፕራይቬታይዜሽን ሂደቱ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ተወያዩ።

አማካሪ ምክር ቤቱ ከወራት በፊት የመንግሥት ኩባንያዎችን በከፊል ወደ ግል የማዛወር ሂደቱን እንዲከታተል የተቋቋመ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በሎጅስቲክስ፣ በቴሌኮም፣ በኃይል ማመንጨትና በሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥ እየሠራች መሆኑን ጠቅሰዋል።

አያይዘውም የምሥራቅ አፍሪካ ውሕደት ለቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ታላቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *