loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን አመራርና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ ቻይና ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል::

በውይይቱ ወቅትም እስከ የፈረንጆች 2018 ዓ.ም መጨረሻ የተጠራቀመ የብድር ወለድን ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘ አስታውቀዋል::

ከዚሁም ጋር የቻይና መንግሥት የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክትን ጠቀሜታ ይረዳል ያሉትፕሬዝዳንት ዥንፒንግ ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል::

ሁለቱም ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር በተለያዩ ዘርፎች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል::

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *