ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በባሌ ዞን በኩታ ገጠም ማሳ ስንዴ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ጎበኙ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በባሌ ዞን በኩታ ገጠም ማሳ ስንዴ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ጎበኙ
አርትስ 30/03/2011
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ በተደረገው ጉብኝት በተጨማሪ ከአርሶአደሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በጉብኝቱ ላይ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌየር ተገኝተዋል።
በባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ አርዳ ቀብሶ ቀበሌ በ2ሺህ350 ሄክታር መሬት ላይ 133 አርሶ አደሮች ያለሙትን የዱረም ስንዴ ማሳ ነው የተጎበኘው።
በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ ተገኝተዋል።