ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቡድን 20 አባል አገራት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቡድን 20 አባል አገራት በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ
አርትስ 21/02/2011
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጀርመን በነበራቸው ቆይታ ከመራሂተ-መንግስት አንጌላ መርከል ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ በበርሊን እየተካሄደ ባለው የቡድን ሀያ አገራት የትብብርመድረክ ላይ ተሳትፈዋል።
ይህ መድረክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ11 የአፍሪካ አገራት በመሰረተ-ልማት፣ በኢንቨስትመንትና ንግድ፣ በፋይናንስ ስርዓት ማሻሻልና ሌሎች የኢኮኖሚ ድጋፎች በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።
መድረኩ አንጌላ መርክልን ጨምሮ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤልሲሲና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመትን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካሀገራት መሪዎች ተሳታፊ የሆኑበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የቡድን 20 አባል አገራት በአገራችን የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በስፋት እንዲሳተፉ ትፈልጋለች ብለዋል።