loading
ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ29፣ 2012 ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ተገለፀ:: ካይሮ ይህን ለማድረግ ያሰበችው በግድቡ አሞላል ሂደት በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የድርድር ሀሳብ መጀመሪያ የውስጥ ምክክር ላድርግበት በሚል ነው ተብሏል፡፡

የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ያቀረበችው አዲስ የመደራደሪያ ረቂቅ ሀሳብ ሀግና መመሪያን ያከበረ አይደለም ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ አክሎም በአዲስ አበባ በኩል የቀረበው ምክረ ሀሳብ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል ህጋዊ መሰረት ይጎድለዋል የሚል ቅሬታ አሰምቷል፡፡ ሄድ መለስ የሚል አቋም የምታሳየው ሱዳን በበኩሏ የግድቡ የደህንት ጉዳይ ያሳስበኛል የሚል ሀሳብ ማንሳት ጀምራለች ነው የተባለው፡፡

በኢትዮጵያ በኩል በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት በተካሄደው ስብሰባ የተደረሰበትን ስምምት የሚጥስ ሀሳብ ቀርቧል በሚል ሰበብ ግብፅና ሱዳን ለጊዜው የአሁኑ ውይይት እንዲቆም ፍላጎት አላቸው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የተፋሰሱን ሀገራት ጥቅም የሚጎዳ ተግባር እንደማትፈፅም በተደጋጋሚ አቋሟን ከመግለፅ ተቆጥባ አታውቅም፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *