ግብረገብነት ያለው ትውልድ ለማፍራት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ ነው::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 ግብረገብነት ያለው ትውልድ ለማፍራት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ ነው:: ግብረገብነት ያለው በስብዕና እውቀት የተገነባ ትውልድ ለማፍራትየስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ ::በአጠቃላይ ትምህርት እየተካሄደ ያለውን ሪፎርምና የቀጣይ አስር ዓመት መሪ እቅድ ዙሪያ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአዳማ ተካሄዷየትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በመድረኩ እንደገለጹት የአጠቃላይ ትምህርት ሴክተር የተማሪዎች መማርና ማንበብ አጠቃላይ ትንተና 43 በመቶ ብቻ ነው
በተለይ የ11ኛና 12ኛ ክፍል የትምህርት እርከን ከዕውቀትና የሙያ ስልጠና ጋር ያልተዛመደ መሆኑንም ጠቅሰዋልይህንን በማስተካከል ግብረገብነትን የተላበሰ በስብዕና እውቀት የተገነባ ትውልድ ለማፍራት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል::
ስርዓተ ትምህርቱ በቴክኖሎጂ ያልተደገፈ ነበረ ያሉት ሚኒስትሩ፣ ትውልዱ ተገቢውን እውቅት፣ ክህሎት፣ እውቅትና ስብዕና እንዳይለበስ ከማድረጉም ባለፈ ለሀገሪቷ የትምህርት ጥራት ውድቀት መንስኤ መሆኑን አመልክተዋልበትምህርት ተቋማት ተደራሽነት ላይ የተከናወነው ስራ የተሻለ ቢሆንም ልዩ ፍላጎት ከሚሹት ውስጥ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ የሆኑት አንድ በመቶ ብቻ እንደሆኑ ጠቁመዋል::