ገቢዎች ሚኒስቴር ህገወጥ ቁሳቁሶችን መያዙን ቀጥሏል
ገቢዎች ሚኒስቴር ህገወጥ ቁሳቁሶችን መያዙን ቀጥሏል
ዛሬ ደግሞ አንድ ራቫ4 መኪና እና 1 ሚሊየን ,287ሺህ, 800 ብር መያዙን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ 1 ሚሊየን,087 ሺህ ,800 ብር የሚገመት የሺሻ እቃ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል ብሏል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በኃሰተኛ ዶክመንት ከትራንስፖርት ባለስልጣን የታርጋ ቁጠር ሊወስድ የነበረ ተጠርጣሪ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከነራቫ4 መኪናዉና በመኪናዉ ዉስጥ ከነበረ 200,000 የኢትዮጵያ ብር ጋር ተይዟል፡፡
የገቢዎች ምንስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ህገ ወጥነት በምንም መልኩ ሊቀጥል አይችልም ፤ህብረተሰቡ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥነትን በመከላከሉ ረገድ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጎን በመቆም እያደረገ ላለዉ ጥቆማና ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡