ጅምሩ የትራምፕ ግምብ ለእይታ በቃ
ጅምሩ የትራምፕ ግምብ ለእይታ በቃ
አርትስ 20/02/18
ገና በፕሬዚዳንትነት የምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት አሜሪካን ከሜክሲኮ በሚለየው ድንበር ላይ ግምብ እሰራለሁ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ወደተግባር ተሸጋግረዋል። የግምቡ ጅምርም ለእይታ በቅቷል።
የሃገር ውስጥ ጸጥታ ጉዳይ ሃላፊዋ ኪርስቲየን ኔልሰን እንዳሉት ወደአሜሪካ የሚገቡ ህገወጥ ስደተኞችን ለማስቆም አስተዳደሩ ማናቸውንም መፍትሄዎች በሙሉ ጥቅም ላይ ያውላል።
ካሊፎርኒያ አቅራቢያ በተገነባው ዘጠኝ ሜትር ከፍታ ባለው ጅምር ግምብ አጠገብ ቆመው መግለጫ የሰጡት ሃላፊዋ ህገወጥ ስደተኞችን ከሃገሪቱ ለማስወጣት የትራምፕ አስተዳደር ያሉትን ህጋዊአማራጮች በሙሉ እየፈተሸ ነው።
ከደቡባዊና ማዕከላዊ አሜሪካ ብጥብጥ እና ድህነትን ሸሽተው ወደአሜሪካ የሚዘልቁ ስደተኞች ዋነኛ መተላለፊያቸው ሜክሲኮ ናት ብለዋል ሃላፊዋ። “በግልጽ ልንገራችሁና ለዚህ መፍትሄው ግምብ መገንባትነው” ነው ያሉት።
ፔንታጎን የትራምፕ አስተዳደር በደቡባዊ የአሜሪካ ድንበር እንዲያሰፍር የጠየቀውን ከ800 እስከ አንድ ሺህ አባላት ያሉት የጦር ሃይል ጥያቄ ተቀብሎ አጽድቋል።