ጃካርታ በሱናሚ አደጋ የጠፉ ዜጎቿን ፍለጋዋን ቀጥላለች፤ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል
ጃካርታ በሱናሚ አደጋ የጠፉ ዜጎቿን ፍለጋዋን ቀጥላለች፤ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል
አርትስ 16/04/2011
በኢንዶዶኔዥያ በተፈጠረው የሱናሚ አደጋ የሞቱ ሰወች ቁጥር ወደ 429 ከፍ ሲል 128 ነዋሪወች የገቡበት አልታወቀም፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የአካባቢው ነዋሪወች አደጋው ከመድረሱ ቀደም ብሎ የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ አለመኖሩ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል፡፡
በአደጋው ምክንያት ከ1 ሺህ 400 በላይ ሰወች የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው በሽወች የሚቆጠሩት ደግሞ ቤት አልባ ሆነዋል፡፡
የጦር ሰራዊት አባላት፣ የመንግስት ሰራተኞች እና በርካታ በጎ ፈቃደኞች በአነፍናፊ ውሾች በመታገዝ የጠፉትን ሰወች በማፈላለግ ስራ ላይ እንደተሰማሩ የአካባቢው ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የደሴቶች ምድር በመባል የምትታወቀው ኢንዶኔዥያ በተደጋጋሚ ለእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እና ለሱናሚ አደጋ የምትጋለጠው የእሳት ቀለበት እየተባለ በሚጠራው የዓለም ክፍል ስለምተገኝ ነው ተብሏል፡፡
አሁን የአካባቢው ነዋሪወች ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት የሚል ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለመገናኛ ብዙሀን ተናግረዋል፡፡
የሀገሪቱ የሚትዎሮሎጂ ተቋምም አደጋው ተመልሶ ሊከሰት ስለሚችል የትኛውም ዜጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቋል፡፡