ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::
ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፉን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል።ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽን ለመከላከል ተግባራዊ ካደረጋቸው የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም ነዉ ድጋፉን ያስረከቡት ፡፡ቫይረሱ በዓለም ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደሯ፤አገራቸው ኢትዮጵያን ለመርዳት ድጋፉን ማድረጓን ገልጸዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ፕሮፌሰርሂሩት፤ሳሙና የእጅ መታጠቢያ 213 ሺህ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትር 50 ያሕል ሰራተኞችችን ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የሚያስች ዋይፋ አፓራተስ አበርክተውልናል። እነዚህ ቁሳቁስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋሞችና ለዩኒቨርሲቲዎች የምናሰራጫቸው ይሆናል።ብለዋልድጋፉ በትምህርት ተቋማት ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡