loading
ዲ.ኤስቲቪ የስፖርት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭቶችን በዚህ ወር ማስተላለፍ እንደሚጀምር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ዲ.ኤስቲቪ የስፖርት ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭቶችን በዚህ ወር ማስተላለፍ እንደሚጀምር አስታወቀ::ዲኤስቲቪ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ የአለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ሊጎች ጨዋታ ወደ ሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሊመጡ መሆናቸውን የገለፀ ሲሆን አዲሱ የሰኔ ወር ለዲ.አስ.ቲቪ እና እስፖርት አፍቃሪ ለሆኑት ደንብኞቹ አስደሳች ዜና ይዞ ብቅ የሚል መሆኑን አስታውቋል ፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ተከትሎ በአለም ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላለፉት የተወሰኑ ወራት ተገድበው የቆዩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ሁኔታዎች መሻሻል እያሳዩ በመምጣታቸው እንቅስቀሰሴዎች ቀስበቀስ ወደ መደበኛው እየተመለሱ ነዉ፡፡ ይህንን ምክኒያት በማረግ ዲ.ኤስ.ቲቪ የሱፐር ስፖርት የቀጥታ የስፖርት ዉድድሮችን ማሰተላለፉን ሊቀጥል ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡ ሶስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች የእንግሊዝ ፕሚየርሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የጣሊያን ሴሪ ኤ እንደገና መጀመራቸውን ባለፈው ሳምንት ማብሰራቸው ይታወሳል፡፡ የስፔን ላ ሊጋ በሱፐር ስፖርት ስክሪኖች ላይ በጁን 11 እንደገና መታየት የሚጀምር ሲሆን በሴቪያ ደርቢ ሴቪያ ከ ሪያል ቤቲስ የሚያደርጉትን ጨዋታ ያስተላላፋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ 9 ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ከሰኔ 12 እስከ 14 ድረስ ይደረጋሉ፡፡ በመቀጠልም ረቡእ ሰኔ 17 ቀን ዉድድሮችን የሚጀምረዉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲሆን ሁለት ውድድሮችን ያደርጋል እነዚህም በታላላቆቹ ክለቦች በማንቸስተር ዪናይትድ እና አርሰናል፣ እንዲሁም አስቶን ቪላ እና ሺፊልድ ዪናይትድ መካካል ይደረጋሉ ብሏል፡፡ የጣሊያን ሲሪ ኤም ከሰኔ 19-21 እንደገና ጨዋታዎቹን የሚጀምር ሲሆን በአውሮፓ እጅግ አስደሳች ከሆኑ ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነውን ውድድር ይዞ ይመጣል ሲል ዴኤስቲቪ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *