ዩጋንዳ እና ሪፓብሊክ ኮንጎ የሚያስተሳስራቸውን መንገድ በጋራ ለመገንባት ተስማሙ፡፡
ዩጋንዳ እና ሪፓብሊክ ኮንጎ በንግድ የሚያስተሳስራቸውን መንገድ በጋራ ለመገንባት ተስማሙ፡፡
የኮንጎው ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሲኬንዲ ሰሞኑን ወደ ካምፓላ ተጉዘው ከዩጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመንገድ ግንባታው ዙሪያ ተመካክረዋል፡፡
አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሁለቱን ሀገራ የሚያገናኘው መንገድ 1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር ይረዝማል፡፡
ዩጋንዳ ከሪፓብሊክ ኮንጎ ጋር የንግድ ትብብሯን ለማጠናከር ይህን ፕሮጀክት የምትሰራው በቅርቡ ከሩዋንዳ ጋር የነበራት ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ከግማሽ ሚሊዮን የማይበልጥ መሆኑን ያወሱት መሪዎቹ ከመንገዱ ግንባታ በኋላ ፈጣን እድገት እንደሚያመጣ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህን በማድረጋቸን መልካም የንግድ ትስስር በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚ እንሆናለን ብለዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ፣ የመሰረተ ልማት እና የፋይናንስ ሚኒስትሮች በቅርቡ ተገናኝተው በግንባታው ዝርዝር ጉዳዩችን ዙሪያ ይወያያሉ ነው የተባለው፡፡
መንገሻ ዓለሙ