loading
ዩኔስኮ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል

አርትስ 1/13/2010
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከኢትየጵያ ጋር ቅርስ ጥበቃና ልማትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ አዲስ የተሾሙትን የዩኔስኮ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አና ኤሊሳ ሳንታና በጽህፈት ቤታቸው ያነጋገሩ ሲሆን በተለያዩ የትብብር አጀንዳዎች ላይ መወያየታቸውን የው ጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት በድረ ገፁ ገልፃôል፡፡
በውይይቱ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች መገኛ መሆኗን ጠቁመው ከዩኔስኮ ጋር ከቅርስ ጥበቃ፣ ጥናትና ምርምር በተጨማሪ ቅርሶቹን ለአለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድም እያደገ የመጣ ትብብር መኖሩን ጠቁመዋል።
የብዝሃ ህይወት ይዞታው አደጋ ላይ ወድቆ የነበረው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከዩኔስኮ ጋር በተደረገ ትብብር መታደግ የተቻለ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ደኤታው በቀጣይም በሁሉም መስኮች ያሉ ትብብሮችን አሟጦ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ዳይሬክተሯ በበኩላቸው በቆይታቸው ከኢትዮጵያ የተለያዩ ተቋማት ጋር ተቀራርበው እንደሚሰሩና በአገራችን በኩል ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ለሚቀርቡ ጉዳዮች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *