loading
የ2018 የካፍ ቶታል ሻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን የሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል::

አርትስ ስፖርት 29/12/2010
ትናንት ሰኞ በግብፅ ካይሮ ይፋ በሆነው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ እና የግብፅ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አሽራድ ሶብሂ እንዲሁም ሌሎች የካፍ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የክለብ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ተከላካይ ማርክ ፊሽ እና የግብፁ ኮከብ ሀዚም ኢማም ደግሞ ስነ ስርአቱን መርተውታል፡፡
በ22ኛው የካፍ ቶታል ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሲሆን፡-
የአንጎላው ፕሪሚየሮ ዴ አጎስቶ ከ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ቲፒ ማዜንቤ፤ የቱኒዚያው ኢስፔራንስ ዴ ቱኒስ ከሌላኛው የቱኒዚያ ክለብ ኢትዋል ዱ ሳህል ጋር ተገናኝተዋል፡፡
የአልጄሪያው ኢ.ኤስ ሴቲፍ ከ ሞሮኮው ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ እንዲሁም የጊኒው ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ ከ ግብፁ አል አህሊ ተገናኝተዋል፡፡
የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታዎች መስከረም 14 እና 15/2018 ሲደረጉ የመልስ ግጥሚያዎች ደግሞ መስከረም 22 እና 23/2018 ይካሄዳሉ፡፡
በ15ኛው የካፍ ቶታል ኮንፌዴሬሽን የሩብ ፍፃሜ ድልድል፡-
የሩዋንዳው ራዮን ስፖርትስ ከ ናይጀሪያው ኢንየምባ፤ የኮንጎ ብራዛቢሉ ካራ ከ ሞሮኮው ራጃ ክለብ አትሌቲክ፤ የግብፁ ኢል ማስሪ ከ አልጄሪያው ዩ.ኤስ.ኤም አልጄር እንዲሁም የዲ.ሪ ኮንጎው ኤ.ኤስ ቪታ ከ ሞሮኮው ቤርካኔ ጋር ይጫወታለ፡፡
ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን መስከረም 16/2018 እንዲሁም የመልስ ጨዋታቸውን ደግሞ መስከረም 23/2018 ያከናውናሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *