የ 2010 የአሸንዳ በዓል ብዛት ያለዉ ቱሪስት የተገኘበት ነዉ ተባለ፡፡
አርትስ 18/12/2010
የዘንድሮዉ የአሸንዳ በዓል ከማነኛዉም ግዜ በበለጠ ከመላዉ አለም የመጡ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በስፋት የተሳተፉበትና ብዛት ያላቸዉ ኤርትራዊያን የተገኙበት መሆኑን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለአርትስ ቲቪ ገልጸዋል፡፤
የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ስለነበርም ግብይቱ እንደተነቃቃ ነግረዉናል፡፡ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ አልባሳት ሽያጭም ከፍተኛ እንደነበር ሰምተናል፡፡ከተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎችም የመጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችም የዘንድሮዉን የአሸንዳ በአል ደማቅ አንዲሆን እንዳደረጉት አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡