loading
የጤናውን ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትን ለማጠናከር  50 ሺህ የጤና ባለሙያዎችን አስተምሮ ማስመረቁን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የጤናውን ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትን ለማጠናከር  50 ሺህ የጤና ባለሙያዎችን አስተምሮ ማስመረቁን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ባለፉት 7 ዓመታት የጤናውን ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትን ለማጠናከር በአሜሪካ ህዝብና መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ሲተገበር የቆየው ፕሮጀክት መርሃ-ግብር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የፍጻሜ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን እንደተናገሩት ፤ፕሮጀክቱ መንግስት የያዛቸውን የጤና ልማት ዕቅዶችን ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አሚር ፕሮጀክቱ ያበረከታቸውን አስተዋጽዎች ሲገልጹ  የጤና ስርዓቱን ከማጠናከርና የህብረተሰቡን ጤና ከማሻሻል አንጻር ለጤና ባለሙያው ሰፊ ግንዛቤ መፍጠሩ፣ የጤናው ዘርፍ የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር የሚመራበት የአስር ዓመት ዕቅድ ማዘጋጀቱ፣ በሃገሪቱ ያለውን የጤና ባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ በተለያየ ደረጃና ዘርፍ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስተምሮ ማብቃቱንና የሰው ሃብትን የተመለከቱ ፖሊሲዎችን እና መርሃ ግብሮችን ለማሻሻል የሚረዱ 24 የጥናት ውጤቶች በስኬት መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዩኤስአይዲ ዳይሬክተር ሌስሌይ ሬድ በመልዕክታቸው እንደገለጹት አዳዲስ የጤና ባለሙያዎች በሚሰሩባቸው የስራ መስኮች ውጤታማ ስራ መስራት የሚያስችሏቸው የክህሎት ስልጠናዎች በፕሮጀክቱ ተካተው እንዲሰጡ መደረጉንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስርዓተ ትምህርትን በመቅረጽ፣ የፋካልቲዎችን አቅም በማጠናከር እንዲሁም ተማሪዎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት በትምህርት ወቅት የተግባር ልምምድ የሚያደርጉባቸውን የቁሳቁስ አቅርቦቶችን ለማሟላት በፕሮጀክቱ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ እንደነበር ተናግረዋል መረጃው የጤና ሚኒስቴር ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *