የጋና መንግስት በሀዘኔ ጊዜ ከጎኔ ለነበራችሁ ምስጋናየ ይድረሳቸውሁ ብሏል
አርትስ 04/01/2011
ለቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን ሞት ሀዘናቸው ለገለጹ ሁሉ ነው የጋና የኢንፎርሜሽን ምክትል ሚኒስትር ኮጆ ኦፖንግ በመንግስታቸው ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡት፡፡
አፍሪካ ኒው እንደዘገበው በኮፊ አና የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት የወቅቱ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ወደ አክራ አቅንተዋል፡፡
በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው የኮፊ አናን ልጅ ኮጆ አናን አባቱ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማትነት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በመግለጽ ለኛም ለሀገሩም ጀግና ነበር የሚል አድናቆቱን አቅርቦላቸዋል፡፡