loading
የገቢዎች ሚኒስቴር በጂጂጋና ቶጎ ጫሌ ኮንትሮባንድን እየተከላከሉ ላሉ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጠ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በጂጂጋና ቶጎ ጫሌ ኮንትሮባንድን እየተከላከሉ ላሉ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጠ፡፡

ሚኒስቴሩ እዉቅናዉን የሰጠዉ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቶጎ ጫሌና ጅግጅጋ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችን ድንገት ባነጋገሩበት ወቅት ነዉ፡፡

ወ/ሮ አዳነችም “ኮንትሮባንድን መፋለም አገርና ህዝብን ከዉድቀት ማዳን ነዉ”ብለዋል፡፡
ሽልማቱም ሞባይሎቹ ዘመናዊ ሳምሰንግ S9( +) ፤ ዘመናዊ ላፐ ቶፕ፤ አንድ ኤፌሳርና ፒክ አፕ መኪኖች ናቸዉ::

የገቢዎች ምንስትሯ በኢትዮጵያ ሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመገኘት ሽልማት ባበረከቱበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ዋናዉ ሽልማታችሁ በስራችሁ ያስመዘገባችሁት ስኬታችሁ ነዉ ፤ለአገርና ለወገን በጥቅማ ጥቅም ሳይንበረከክ የሰራ ሽልማት ይገበዋል፤ በስራችሁም ኮርተናል፤ ብለዋል፡፡
በቶጎ ጫሌ ሰሞኑን 60ሚሊየን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *