loading
የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተኛ መጠን ያለው የስንዴና ዘይት ግዢ ተፈጸመ:: ግዥው የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ከማስፍን አንጻር የዋጋ ግሽበትን የመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ፋይዳ እንዳለው የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጸው የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቶ ቀናት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡


ባለፉት ጥቅምትና ህዳር ወራት የ4 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ግዥ የተከናወነ ሲሆን ፤ከዚህ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ወደ ሃገር ውስጥ የገባ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ ቀሪውም በተቻለ ፍጥነት ተጓጉዞ ወደ ሀገር ውስጥ አንደሚገባም የተገለጸ ሲሆን ፤ የ12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዢ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡


ከዚሁ ጋር በተያያዘም የምግብ ዘይትና ዱቄት ከውጭ አስመጪዎች በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገቡ በመደረጉ የሸቀጦች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ማስቻሉም ተገልጿል፡፡ በመሆኑም በጥቅምት ወር የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በህዳር ወር ቅናሽ ማሳየቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ መረጃውን ያገኘነው ከገንዘብ ሚኒስቴር ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *