loading
የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ በኢትዮጵያ የስልጠና ማዕከል በሚከፍትበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ::

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው የባየርን ሙኒክ በኢትዮጵያ የስፖርት ስልጠና ማዕከል መክፈት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ቢርታ ወጊኔር ጋር ዉይይት አድርገዋል ሲል የስፖርት ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገፅ አስነብቧል።

አምባሳደሯ የጀርመን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በማንኛዉም የልማት መስክ ላይ በትብብር የሚሰራ መሆኑን ገልፀዉ፤ በስፖርቱ መስክ ወደ ስራ መግባት የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተዘጋጅቶ በሚያዚያ ወር ከጀርመን ከሚመጡ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊና የስፖርት ክለብ ባለሙያዎች፤ ከስፖርት ኮሚሽን ጋር ለመፈራረም ዝግጅት እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደ ስፖርት ኮሚሽን መረጃ ኮሚሽነር አቶ እርስቱም ጀርመን በሌሎች የሀገሪቱ ልማት ላይ የምታደርገዉን የጋራ የትብብር ስራዎችን፤ በስፖርቱም ተግባራዊ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸዉ ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *