loading
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ:: ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ይህን ያሉት በሳቸውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲዎች መካከል አለመግበባት በመፈጠሩ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በፓርላማው ብዙ መቀመጫ ያላቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ካቢላ ደጋፊዎችና ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚያስተዳድረው የሺሴኬዲ ፓርቲ ፖለቲካዊ ልዩነታቸውን ማስታረቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡

በመሆኑም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋት ጥምረት ለማድረግ መወሰናቸውን ነው ፕሬዚዳንት ሺሴኬዲ ይፋ ያደረጉት፡፡ ሺሴኪዲ በመግለጫቸው ለሁለት ዓመት ያህል ያለመታከት ያደረግንው ጥረት ውጤት አልባ በመሆኑ ብናዝንም አሁን ያለው አማራጭ ወይ አዲስ ጥምረት መመስረት አልያም ፓርላማውን በትኖ አዲስ
ምርጫ ማካሄድ ነው ብለዋል፡፡

እንደአውሮፖዊያኑ አቆጣጠር በ2019 ከተጓተተ ምርጫ በኋላ ሺሴኬዲ ወደ ስልጣን ሲመጡ በሚስጥር ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ካቢላ ጋር የጥምር መንግስት ለመመስረት አቅደው ነበር ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የአሁኑ ውሳኔ ላይ ከመድረሳቸው አስቀድመው በርካታ ፓርቲዎና ታዋቂ ግለሸቦችን ማማከራቸውን ገልፀዋል፡፡ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣተር በ1960 ከቤልጂየም ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ወዲህ የመጀመሪያው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የተካሄደው ሺሴኬዲ ያሸነፉበት ምርጫ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *