የደብረማርቆስ ነዋሪዎች ለ20 ዓመታት ጠብቀው ያቆዩላቸውን ንብረት ለኤርትራዊያኑ አስረከቡ
አርትስ 14/01/2011
ከ20 ዓመታት በፊት ኑሯቸውን በደብረ ማርቆስ ከተማ አድርገው የነበሩት ኤርትራዉያን ፤የወቅቱ አስከፊ የፖለቲካ ውሳኔ ከቤት ንብረታቸዉ እንዲፈናቀሉ አድርጓቸዉ ነበር ፡፡
ኤርትራዉያኑ ከ 20 ዓመት በኋላ ወደ ደብረማርቆስ ሲመለሱም የደብረማርቆስ ነዋሪ ደንኳን ጥሎ ደግሶ በናፍቆት እያነባ ተቀብሏቸዋል፡፡
ኤርትራዉያኑ አቶ ተስፋ ሚካኤል ግደይና አቶ መድሃኔ ግደይ ወደ ቀድሞ ከተማቸው ሲመለሱ ከ20 ዓመት በፊት ትተዉት የሄዱትን ቤታቸዉንና ንብረታቸዉን በአደራ ጠብቀዉ አስረክበዋቸዋል፡፡