loading
የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ ሪክ ማቻር ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይገባሉ

የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ ሪክ ማቻር ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይገባሉ

አርትስ 21/02/2011


የደቡብ ሱዳን አማጺ መሪ ሪክ ማቻር ከዚህ ቀደም የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በዛሬዉ ዕለት ወደ አገራቸው እንደሚገቡ የአማጺ ቡድኑ ቃል አቀባይ ገለጸ፡፡

የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር በስደት ከሚኖሩበት አገር ወጥተው ከጥቂት ልዑኮቻቸው ጋር ወደ ዋና ከተማዋ ጁባ እንደሚገቡ ቃል አቃባይ ላም ፓውል ገብሬል ለአሶሺትድፕሬስ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር በሁለቱም ወገን መተማመን ሊኖር እንደሚገባ ቃል አቃባዩ አሳስበዋል፡፡

በአዲሱ ስምምነት መሰረት ሪክ ማቻር እንደገና የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የተፈጸሙ ሁለት ተመሳሳይ ስምምነቶች በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ተግባራዊ መሆን አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *