የዚምባቡየ ተቃዋሚዎች ለፕሬዝዳንቱ ንግግር እውቅና አንሰጥም አሉ
አርትስ 9/1/2011
ተቃዋሚዎቹ በአወዛጋቢ የምርጫ ውጤት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የመጀመሪያ የምክር ቤት ንግግራችን ሲያደርጉ ነው ፓርላማውን ረግጠው የወጡት፡፡
ሮይተርስ ከሀራሬ እንደዘገበው በኔልሰን ቻሚሳ የሚመሩት የምክር ቤት አባላቱ ይህን ንግግር ተቀምጦ ማዳመጥ ህጋዊነት ለሌለው ፕሬዝዳንት እውቅና መስጠት ነው ብለዋል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቱ የፕዝዳንቱን ንግግር አቋርጠው በወጡበት ወቅት የሹፈት ቃላት በመሰንዘር ሁካታ ፋረው ነበር ተብሏል፡፡
ፕዝዳንቱ በመጀመሪያ የምክር ቤት ንግግራቸው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚሻሻልበት አሰራር ላይ የበለጠ ትኩረት አድርገው ህዝቡ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የምርጫው ቀንደኛ ተፎካካሪ የነበሩት የሙቭመንት ፎር ዲሞክሰራሲ ፓርቲ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ አሁንም በምርጫው ተጭበርብረናል ሀገሪቱ የምትመራው ህጋዊ ባልሆነ ፕሬዝዳንት ነው በሚለው አቋማቸው እንደጸኑ ናቸው፡፡