የዘንድሮው የሻደይ በዓል ከነሐሴ 16 እስከ 18 በዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን” ሻዴይ በዓላችን ለገጽታ ግንባታችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል፡፡
የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ተክሉ ለአርትስ እንደገለጹት በዓሉ በሁሉም ወረዳዎች በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል ፡፡
ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን በሰቆጣ ከተማ የባህል ሲምፖዚየም የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ታምራት ላይኔ በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡