loading
የውጭ አገር ህጋዊ የስራ ስምሪት በመስከረም ወር ይጀመራል፡፡

አርትስ 30/12/2010
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በድረገጹ እንደገለፀው ለአመታት ታግዶ የነበረው ህጋዊ የውጭ አገራት የስራ ስምሪት በ2011 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ እንደሚጀመር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡
በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ አገር ስራ ስምሪት ዳይሪክተር ጀነራል አቶ ብርሀኑ አበራ እንደገለፁት ስምሪቱ እስካሁን የዘገየው ስምሪት ከሚደረግባቸው አገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረግ አስፈላጊ ስለነበረ እና የዜጎችን ደህንነትና ክብር ለማስጠበቅ ከተቀባይ አገራት ጋር የሚደረገው ስምምነት ወሳኝ በመሆኑንም ነው ተብሎል፡፡
ህጋዊ የስራ ስምሪትን ለማሳለጥ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ባሻገር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራትን ይጠይቃልም ተብሎዋል፡፡
አዋጁ በ2008 ዓ.ም ቢፀድቅም እስከ አሁን ተግባራዊ ሳይሆን እንደቆየ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የዜጎችን የስራ ስምሪት አስመልክቶ ከሳኡዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ጆርዳን ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በመደረጉ የስራ ስምሪቱ በ2011 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ እንደሚጀመር ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *