የኮንጎ የምርጫ ውጤት ሊዘገይ ይችላል ተባለ
የኮንጎ የምርጫ ውጤት ሊዘገይ ይችላል ተባለ
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ከ59 ዓመት በኋላ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረግበታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመጀመሪያው ምርጫ ውጤቱ የሚገለፅበት ቀን ሊራዘም እንደሚችል ተነግሯል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እስካሁን የምርጫው የድመፅ ቆጠራ ውጤት 17 በመቶ ብቻ ነው የደረሰው፡፡
የኮሚሽኑ ፕዝረዳንት ኮርኔል ናንጋ በተቻለን አቅም የምርጫው ጠቅላላ ውጤት በፍጥነት እንዲደርስን ለማድረግ እንሞክራለን ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ የምርጫ ውጤቱን ለህዝ ለማሳወቅ ምን ችግር እንደገጠማቸው በዝርዝር የተናገሩት ነገር የለም፡፡
በምርጫው በተቃዋሚ ጎራ ለፍክክር የቀረቡት ፌሊክስ ሺሲኬዲ በቃል አቀባያቸው በኩል እንዳሉት የምርጫው ውጤት መዘግየት ሳይሆን የሚያሳስበን ታአማኒነቱ ነው ብለዋል፡፡
ከደቡባዊ አፍሪካ ልማት በማህበረሰብ የተወከሉ የምርጫ ታዛቢዎች በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ላይ በአንፃራዊነት ሰላማዊ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ውጤቱም ልክ እንደ ድምፅ አሰጣጡ ሂደት ሰላማዊ እንደሆን ተስፋውን የገለፀው የታዛቢ ቡድኑ አሁን በዚህ መልኩ ምርጫ መካሄዱ በራሱ ትልቅ ድል ነው ብሏል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በኢቦላ መከሰት እና በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኮንጓዊያን በምርጫ አልተሳተፉም፡፡