loading
የኮቪድ 19 ክትባት ተስፋና ስጋት በኢትዮጵያ በሚል ርእሰ ውይይት ተካሄደ።

አዲስ አበባ፣ጥር 30፣ 2013  የኮቪድ 19 ክትባት ተስፋና ስጋት በኢትዮጵያ በሚል ርእሰ ውይይት ተካሄደ። በዶክተር እናውጋው መሀሪ መስራችነት የተቋቋመው ፒፕል ቱ ፒፕል በጎ አድራጎት ድርጅት እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አድቮኬሲ ካውንስል ኦን ኮቪድ 19 አማካኝነት በዌቢናር ነው ውይይቱ የተካሄደው ። በውይይቱ የኮቪድ 19 ክትባት ተስፋና ስጋት በኢትዮጵያ ምን ይመስላል ፧የሚለው ጉዳይ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል።

የዲያስፖራው ሚናም ምን መሆን አለበት የሚለው ጉዳይ በውይይቱ ተነስቷል ። በውይይቱ የተሳተፉት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጽም አረጋ የውይይቱን አዘጋጆች እና ተሳታፊዎች አመስግነዋል ።መዘግየት ያልነበረበት ውይይት ብለውታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *