loading
የኮሮና ቫይረስ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው መንደሮች እንዳይገባ ልንረባረብ ይገባል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው መንደሮች እንዳይገባ ልንረባረብ ይገባል ተባለ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  የኮሮና ቫይረስን  እና  የሕዳሴው ግድብ ግንባታን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት  አንደኛው  የሀገራችን ፈተና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ቫይረሱ የሚተላለፍበት መንገድ ከሰዎች ለሰዎች ንኪኪ ጋር የተገናኘ እና የሚስፋፋበትም መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ ፈጣን እየሆነ እንደመጣ በየዕለቱ የምናየው እውነታ መሆኑነም ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወረርሽኙ 201 ሀገራትን አዳርሷል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸዉ።በሀገራችን የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 29 ቢሆንም በሚቀጥሉት ሳምንታት ቁጥሩ ሊያሻቅብ ይችል ይሆናል። ምናልባትም ሞት ያጋጥመንም ይሆናል ብለዋል ጠቅላ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸዉ፡፡አሁን በሽታው ከአዲስ አበባ አልፎ በክልል ከተሞችም እየታየ ነው። ለቁጥጥር እንዳያስቸግር አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሚኖሩባቸው መንደሮች እንዳይገባ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በመንግሥት በኩል የጥንቃቄ ሕጎችን በጥብቅ ለማስፈጸም፣ የመከላከያና የሕክምና ቁሳቁሶችን በየቦታው ለማዳረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ  መሆኑነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታዉሰዋል፡፡
ለኮሮና ሲባል ቤት ውስጥ መቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ኪሳራዎችን ሊያደርስብንም ይችላል፤ ሆኖም ግን በሌላ መልኩ ካየነው ይሄንን አጋጣሚ ለመልካም ተግባራት ልናውለው እንችላለን ብለዋል፡፡ከመልካም ተግባራቶቹም መካከል  ወላጆች ለልጆቻቸው ፍቅር የሚሰጡበት፤ ባለትዳሮች ስለቀጣይ የሕይወታቸው ምዕራፍ በሰፊው የሚያቅዱበት፤ እንዲሁም ማንበብ የሚፈልጉ ሰዎች ጊዜ ወስደው እንዲያነብቡ፤ የሚጽፉ ሰዎች ጊዜ አግኝተው እንዲያሰላስሉ፣ የሚመራመሩ ሰዎች እንዲመራመሩ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አንስተዋል፡፡

በዚህ መልኩ ለተወሰነ ጊዜ ወደ ውጭ ከመውጣት ተቆጥበው ቤታቸው የሚያሳልፉ ዜጎቻችን ራሳቸውንና ሌሎችንም ከክፉው ወረርሽኝ ከማዳን በዘለለ፣ ወረርሽኙ አልፎ ሁሉም ነገር ሲረጋጋ ብዙ መልካም ነገሮችን ማትረፋቸው አይቀርም ሲሉ  በመልዕክታቸዉ ጠቁመዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *