የኬንያ ጎዳናዎች የሞት መንገዶች ሆነዋል ተባለ
አርትስ 30/1/2011
በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ብቻ በኬንያ 2 ሺህ 345 ሰዎች በመንገድ ላይ አደጋ ህይወታቸው አልፏል፡፡
ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው በኬንያ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው የሚያልፍ እና አካላቸው የሚጎድል ዜጎች ቁጥር በስምንት በመቶ ጨምሯል፡፡
የሀገሪቱ የትራፊክ ደህንነት ሀላፊ ሳሙኤል ኪሙራ በአስደንጋጭ ሁኔታ እጨመረ የመጣው የትራፊክ አደጋ ኬነያን እያሳሰባት ነው ብለዋል፡፡
በተለይ ቦዳ ቦዳ በመባል የሚታወቁትን የሞተር ሳይክሎች የሚነዱ አሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎቻቸውን የራስ ቅል መከላከያ እንዲያደርጉና የትራፊክ ህጎችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል ሃላፊው፡፡
በዛሬው እለት እንኳ በኬንያ መንገደኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ አውቶቡስ ላይ በደረሰ አደጋ በትንሹ50 ሰዎች ህይዎትሳይሞቱ እንዳልቀሩ አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡
የኬንያ መንግስት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2013 የአደጋው አስከፊነት ቢያሳስበው በምሽት የአውቶቡስ ጉዞ እንዳይደረግ እስከመከልከል ደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡