የኬንያ ጋዜጣ በኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ለውጥ የኬንያን ኢንቨስትመንት እያሸሸ ነው አለ
የኬንያ ጋዜጣ በኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ለውጥ የኬንያን ኢንቨስትመንት እያሸሸ ነው አለ
አርትስ 20/02/2011
በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሃገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ኬንያ ቀዳሚ ናት ያለው ስታንዳርድ ሚዲያ የተባለው የኬንያ ትልቁ ጋዜጣ በኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ለውጥ ግን ወደ ቀጠናውየሚመጡ የውጭ ባለሀብቶችን እያሸሸባት መሆኑን ተናግሯል።
ጋዜጣው በጉዳዩ ላይ የተደረገ ጥናትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉት ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ማሻሻያዎች የውጭ ባለሀብቶች ፊታቸውን ከኬንያ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያዞሩ እያስገደደዳቸው ነው ብሏል፡፡
በመሆኑም ኬንያ በዘርፉ የነበራት መሪነት ከኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር በመጥበብ ላይ እንደሆነና በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በኬንያ ላይ ብልጫእንደምትወስድ ነው ጥናቱ ያመለከተው፡፡
ጋዜጣው አርነስት ኤንድ ያንግ የተባለው ኩባንያ ያቀረበውን ጥናት ተመርኩዞ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት በአየር መንገድ፣ በቴሌኮም፣ በኃይል ማመንጫና ሎጅስቲክን የማጓጓዝ አገልግሎትን ለግሉዘርፍ ክፍት እንደሚያደርግ ማሳወቁን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍስት ጨምሯል።
ኢትዮጵያ 62 የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በመሳብ ከአፍሪካ በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡