loading
የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2011 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል
አርትስ 03/01/2011
በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2011 ዘመን በመደበኛ ሆነ መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ 295 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርታቸውን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው እንዲከታተሉ መወሰኑን ገልጿል፡፡
በመደበኛ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲማሩ የተወሰነላቸው ተማሪዎች ቁጥር 149 ሺህ 823 ሲሆኑ ከነዚህም መካከል 98 ሺህ 567 የተፈጥሮ ሳይንስ 51 ሺህ 256 የሚሆኑት የህብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡
በዚህም በመደበኛ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት የ2011 የመግቢያ መስፈርት መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 362 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 345 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡
መደበኛ እና የማታ በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 345 እና ከዚያ በላይ ለሴት 335 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡
ለታዳጊ ክልል ተማሪዎች፣ አርብቶ አደር አካባቢ ተወላጆች እና በፀጥታ ምክንያት ትኩረት የተሰጣቸው ተማሪዎች መግቢያ ውጤት ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 345 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለሴት 330 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 335 እና ከዚያ በላይ እና ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ለግል ተፈታኞች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 375 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 370 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በህብረተሰብ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 375 እና ከዚያ በላይ ለሴት 370 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡
መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ለወንድ በተፈጥሮ ሳይንስ 275 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴት 265 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በህብረተሰብ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 275 እና ከዚያ በላ ለሴት 265 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡
እንዲሁም ለዐይነስውራን ተማሪዎች በህብረተሰብ ሳይንስ ለወንድ 210 እና ከዚያ በላይ ለሴት 200 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *