የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እርቅ ፈፀሙ
የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እርቅ ፈፀሙ
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በዛሬው እለት በይፋ በአምቦ ከተማ የእርቅ ስነ ስርዓት ፈጽመዋል።
የኦሮሞ አባ ገዳዎች ባዘጋጀው የእርቅ ስነስርአቱ በአምቦ ከተማ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል፡፡
በእርቅ ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ወጣቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች እንዲሁም የአምቦ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይም በኦሮሞ ባህል መሰረት ኮርማ በሬ በማረድ በይፋ የእርቅ ስነ ስርዓት ፈጽመዋል።
በእርቅ ስነ ስርዓቱንም ከኦሮሚያ ክልል መንግስት በኩል ዶክተር ሚልኬሳ ሚደቅሳ ከኦነግ በኩል የግንባሩ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ተገኝተው ፈፅመዋል።
ሁለቱም አካላት ከዚብ ሀኋላ ወደ ደም መፋሰስ እንደማይገቡ እንዲሁም ያለፈውን ነገር በመተው ስለወደፊቱ ብቻ በጋራ ለመስራት በእርቅ ስነ ስርዓቱ ቃል ገብተዋል።