የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች በአካባቢያቸው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የምግብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች በአካባቢያቸው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የምግብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ:: የእንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት አካባቢ ተወለጆች የኮቪድ 19 በሽታ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል በአካባቢያቸው ለሚገኙ ከ 3 መቶ በላይ ለሚሆኑ ድጋፍ ፈላጊዎች የምግብና የአይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የወጣቶቹ አስታባበሪ አቶ አሳልፈው ጌትነት ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ለወገናቸው ፈጥነው በመድረስ በአካቢያቸው የሚኖሩና የከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙትን በመለየት ግምታዊ ዋጋቸው ከ86 ሽህ ብር በላይ የሚገብ ቁሳቁሶችን መለገሳቸውን ድጋፉ ከተደረጋለቸው ሰዎች ሰምተናል ፡፡ ደምፅ…2
በተመሳሳይም የወቅትኑ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ደም ለሚስፈልጋቸው ህሙማን ደም የመለገስ መረሃ ግብር ማድረጋቸውን አካባቢዉ ወጣት መኳንት ስንታየሁ ተናግሯል ፡፡በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤፍሬም አሩሲ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መዓድ ማጋራት ጥሪ በመቀበል በአካባቢው ወጣቶች ስራዎች መካነወናቸውን በመግለፅ ከዚሁ ጎን ለጎን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ማከናወናቸውን ነው የጠቀሱት::ለድጋፍ የተበረከተው ገንዘብ በውጪ ሃገር ከሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች እና አቅም ካላቸው ሰዎች መሰብሰቡ ሰምተናል፡፡