የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ (ካራባዎ ዋንጫ) የአራተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አርትስ ስፖርት 21/02/2011
በካራባዎ ዋንጫ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን በርንማውዝ 2 ለ 1 ኖርዊች ሲቲ፤ ቡርቶን አልቢዮን 3 ለ 2 ኖቲንግሀም ፎረስትበሆነ ውጤት ሲለያዩ፤ በኪንግ ፓወር ሌስተር ሲቲ ከ ሳውዛምፕተን ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በሌስተሩ ባለሀብት ቪቻይ ሞት ምክንያት ለሌላጊዜ ተላልፏል፡፡ ዛሬ ደግሞ ምሽት 4፡45 ላይ በተመሳሳይ ስዓት በኢምሬትስ አርሰናል ከ ብላክፑል፤ በስታንፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከ ደርቢ ካውንቲእንዲሁም በለንደን የኦሎምፒክ ስታዲየም ዌስት ሀም ዩናይትድ ከ ቶተንሀም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ምሽት 5፡00 ላይ ደግሞ ሚድልስብራ ከክሪስታል ፓላስ የሚገናኙ ይሆናል፡፡ በዚህ ውድድር ለወጣቶች ሰፊ ዕድል የሚሰጥበት እንደመሆኑ ተስፋ ያላቸው ኮከቦች በአሰልጣኞችየሚገመገሙበት ነው፡፡