loading
የእንግሊዝ ቡድኖች በአውሮፓ የውድድር መድረክ የበላይነታቸውን ማሳየታቸውን ቀጥለዋል

የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ግጥሚያዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከተሞች ተከናውነዋል፡፡

ወደ ኔፕልስ ጣሊያን ያመራው አርሰናል ሳን ፓውሎ ላይ ናፖሊን 1 ለ 0 በመርታት ፤ በድምር ውጤት 3 ለ 0 ድል አድርጎ የግማሽ ፍፃሜውን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

ለመድፈኞቹ ብቸኛዋን የአሸናፊነት ጎል አሌክሳንደር ላካዜት ከቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚደረገው የዙር ጨዋታ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ ቫሌንሲያን ያስተናግዳል፡፡

ቼልሲ ደግሞ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ስላቪያ ፕራሃን ገጥሞ 4 ለ 3 በመርታት በድምር ውጤት 5 ለ 3 ውጤት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

በርካታ ጎሎች በተቆጠሩበት የዚህ ጨዋታ ላይ የሰማያዊዎቹን ጎሎች ስፔናዊው ፔድሮ ሩድርጌዝ ሁለት እንዲሁም ሲሞን ደሊ በራሱ መረብ ላይ እና ኦሊቪዬ ዥሩ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡  

የማውሪዚዮ ሳሪው ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የጀርመኑን አይንትራክት ፍራንክፉርት የሚገጥም ይሆናል፡፡

ቫሌንሲያ ሜስቲያ ላይ ቪያሪያልን በቶኒ ላቶ እና ዳንዬል ፓሬሆ ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፎ ቀጣዩን ዙር በ5 ለ 1 ውጤት ሲቀላቀል፤ አይንትራክት ፍራንክፉርት ሜዳው ላይ የፖርቱጋሉን ቤንፊካ 2 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 4 ለ 4 ቢለያይም ከሜዳው ውጭ ጎል ባስቆጠረ በሚለው ህግ ተጠቃሚ ሆኖ ቀጣዩን ዙር ተዋህዷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *