የእንቦጭ አረምን መከላከል የሚያስችል ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
አርትስ 03/01/2010 ዓ.ም
የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ እንደገለፀው በውይይቱም በዋናነት በጣና ሀይቅ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የእንቦጭ አረም መፍትሔ ማምጣት የሚችሉ ጥናትና ምርምሮች ቀርበዋል፡፡ በውይይቱ ከሀገር ውስጥና ከወጭ ሀገራት የተወጣጡ ተመራማሪዎች እና አምባሳደሮች ተገኝተውበታል፡፡
ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከስምንት በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርቡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አረሙ ከጣና ሀይቅ በተጨማሪ በዝዋይ፣በአባያ ሀይቅ፣በቆቃ ግድብ እና በባሮ ወንዝ ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አውደጥናት ላይ ባደረጉት ንግግር ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ጣናን መታደግና ሌሎች የሀገሪቱን ውሃማ አካላት ከእንቦጭ መጠበቅ ይገባናል ብለዋል፡፡