loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራል

የሊጉ የሁለተኛው ዙር ሁለተኛ ሳምንት ግጥሚያዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በክልል ስታዲየሞች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

ባለፈው ሳምንት በባህር ዳር ሽንፈት አስተናግዶ የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ በአዲስ አበባ ስታዲየም አዳማ ከተማን 11፡00 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል፡፡ ጊዮርጊስ ከመሪው መቐለ ያለው የነጥብ ልዩነት 12 የደረሰ ሲሆን አሸንፎ ቡድኑን ወደ ውጤታማነቱ ለመመለስ የዛሬውን ግጥሚያ ውጤት በእጅጉ ይፈልገዋል፡፡

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አርቢትር በላይ ታደሰ ይመሩታል ተብሏል፡፡

በነገው ዕለት በድል ጉዞ ላይ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ሀዋሳ ላይ ከድሩዳዋ ከነማ 9፡00 ሰዓት ሲጫወት፤ በስዩም ከበደ የሚሰለጥነው መከላከያ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ጅማ አባ ጅፋርን ይገጥማል፡፡

በዕለተ ዕሁድ ደግሞ በተመሳሳይ 9፡00 ሰዓት ሶስት ግጥሚያዎች ይደረጋሉ፤ የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ በትግራይ ስታዲየም ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ያስተናግዳል፡፡

ፋሲል ከነማ ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ሀዋሳ ከተማን ሲያገኝ፤ ስሑል ሽረ በሽረ ስታዲየም ባህር ዳር ከነማን ያስተናግዳል፡፡

በ17ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕሁድ ከደደቢት ጋር ሊያካሄደው የነበረው ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል፡፡

ሰኞ የሳምንቱ መዝጊያ ፍልሚያ በሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ 70 እንደርታ በ38 ነጥብ ይመረዋል፤ ሲዳማ ቡና በ30 ይከተላል ፤ ፋሲል ከነማ በ28 ሶስተኛ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *