loading
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ በይፋ ስራ መጀመሩን በተመለከተ በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስትሮች፣ የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና ምከትል ዋና ዳይሬክተር ሙሀመድ እንድሪስ፣ የክልል መስተዳደር ተወካዮች፣ የዳያስፖራ ማህበር አመራሮች፣ የዓለም አቀፍ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ እና የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሙሀመድ እንድሪስ የኤጄንሲውን ድህረ ገጽና የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይዘት በተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚሁ መሰረት

የኤጄንሲው ድህረ ገጽ – www.ethiopiandiasporaagency.org
የኤጄንሲው ፌስ ቡክ ገጽ – @ Diaspora Agency
የኤጄንሲው ቲዊተር ገጽ -@ Diaspora Agency
የኤጄንሲው ዩ ቱዩብ ገጽ – Ethiopian Diaspora Agency በመሆን ይፋ ተደርጓል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *