loading
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ለደንበኞቼ ቀልጣፋ አገልግሎት ተዘጋጅቻለሁ አለ

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎትደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ

ድርጅቱ 13 ዘመናዊ የኮንቴይነር መጫኛና ማውረጃ ማሽኖችን ለስራ ማዘጋጀቱ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት 95 በመቶው የሀገሪቱ ገቢና ወጪ ንግዶች ይከናወኑበታል፡፡ በሰባት ደረቅ ወደብና ተርሚናሎች ነው እያገለገለ የሚገኘው፡፡

ድርጅቱ በ11 የኢትዮጵያ መርከቦች ከ306 ያላነሱ የተለያዩ ሀገራት ወደቦችን በማዳረስ ዕቃዎችን ያጓጉዛል፡፡

የድርጅቱ የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ አሸብር ኖታ እንደተናገሩት ዕቃዎች ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ እየተሰጠ ያለው የተጓተተ አገልግሎት ግን ደንበኞችን እያማረረ ነው፡፡

የኮንቴነር መጫኛና ማውረጃ ማሽኖች እጥረትና ብልሽት ደግሞ ለመጉላላቱ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍም 13 የመጫኛና የማውረጃ ማሽኖች ተገዝተው ሞጆ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡

ይህም አንድ ዕቃ ከወደብ ለማውጣት እስከ 40 ቀናት ይወስድ የነበረውን አገልግሎትም ከ2 እስከ 3 ቀናት ባነሰ ጊዜ ያሳጥረዋል  እንደሃላፊው መግለጫ።

ከ13 ማሽኖች ውስጥ አስሩ ለሞጆ ደረቅ ወደብና ተርሚናል የተመደቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ሶስቱ ደግሞ ለቃሊቲ፣ለመቀሌ እና ለድሬዳዋ ደረቅ ወደብና ተርሚናሎች ነው ተመድበዋል ተብሏል።

ማሽኖቹ መጪው ቅዳሜ እንደሚጀምሩም ተነግሯል።ዜናው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *