loading
የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች እና እየተባባሰ የመጣውን ስርዓት አልበኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን አሉ፡፡

የሀይማኖት አባቶቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነዉ፡፡
የሃይማኖት አባቶቹ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅጅጋ ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሰው ህይወት መጥፋቱ እና አብያተ ክርስቲያናት መቃጠል የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ነዉ ብለዋል፡፡
በተያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው ስርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት የሃማኖት አባቶቹ መንግስት አጥፊዎችን በመቅጣት ህግ እና ስርዓት ሊያስከብር ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡
ወጣቶች ከስሜታዊነት ወጥተው ቆም ብለው በሰከነ አዕምሮ የሀገራቸውን ሰላምና አንድነት እንዲያስጠብቁ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በተለያየ ጊዜ በግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የተናገሩት የሃይማኖት አባቶች በቀጣይም ድጋፋቸው እንደማይቋረጥ አሰታውቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *