የኢትዮጵያ ክህምና ማህበር ለሕክምና ባለሙያዎች ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ ወጪ መንደር ልገነባ ነው አለ
የኢትዮጵያ ክህምና ማህበር ለሕክምና ባለሙያዎች ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ ወጪ መንደር ልገነባ ነው አለ
አርትስ 25/03/2011
የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2.4 ቢሊዮን ዶላር ለ7 ሺህ የሕክምና ባለሙያዎች ቤት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ ሪዞርትና መናፈሻ ያካተተ መንደር በአዲስ አበባ እንደሚገነባ አስታውቋል፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገሚቺስ ማሞ እንደገለጹት፣ የግንባታው ሥራ የሚከናወነው በሁለት ዕርከን ሲሆን፣ በመጀመርያው ዕርከን የሚከናወነው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ነው፡፡
የቤቶቹ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኃላ በሁለተኛ ዕርከን የሆቴል፣ የሪዞርትና የመናፈሻ ግንባታ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ለ30 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ግንባታውም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል፡፡
ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላም ለሕክምና ባለሙያዎች የሚከፋፈለው በግዥ ነው፣ ግዥውም የሚፈጸመው በረዥም ጊዜ በሚከፈል ብድር መሆኑ ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባው የመንደር ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ በእያንዳንዱ ክልል ርዕስ ከተማ ቢያንስ ለ500 የሕክምና ባለሙያዎች የሚውል መኖሪያ ቤት የመገንባት ዕቅድ መኖሩንም ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል፡፡