የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት በደረሰዉ የሰዉ ህይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም ማዘንዋን ገለጸች፡፡
ቤተክርስትያንዋ ሀዘንዋን የገለጸችዉ ዛሬ የተጀመረዉን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ ለአርትስ ቲቪ በላከችዉ መግለጫ ነዉ፡፡
በመግለጫዉ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀጳጳስ ካርዲናል ብርሃነየሱስ እንዳስታወቁት የፍልሰታ ጾም የተጀመረዉ ቤተክርስትያናችን 19ነኛዉን የአመሰያን ጉባኤ በስኬት ባስተናገደች ማግስት በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል፡፡
ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተዉ ግጭት ምክንያት የሰዉ ህይወት በማለፉ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡ቤተክርስትያንዋም ለሰላም ትጸልያለች ብለዋል፡፡
ካርዲናሉ በመግለጫቸዉ በአሁኑ ወቅት ምእመናንም በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉና በቤታቸዉም ሆነዉ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በመደገፍ ጻሙን ልናሳልፍ ይገባል ብለዋል፡፡