loading
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሲሸልስ ዋናውን ቡድን አሸንፏል

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሲሸልስ ዋናውን ቡድን አሸንፏል

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን (ኦሊምፒክ ቡድን) ማረፊያውን በሸበሌ ሆቴል በማድረግ 34 ተጫዋቾችን በመያዝ ለማሊ የኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታ ጨዋታው ዝግጅት ላይ ሲሆን የሲሸልስ ዋናው ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለበት የመጨረሻ ጨዋታ በአዲስ አበባ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።
ሁለቱ ቡድኖች ሁለት የወዳጅነት ግጥሚያቸውን የሚያደርጉ ሲሆን የመጀመሪያውን ጨዋታ በትናንት ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም አካሂደው ኢትዮጵያ 1 ለ 0 ድል አድራጋለች፡፡

ባለፈው ዕሁድ ከኢትዮጵያ ውደ ኬንያ ይበር በነበረው አውሮፕላን በደረሰው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የህሊና ፀሎት በማድረግ በተጀመረው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ነስሩ 5ኛው ደቂቃ ላይ ከመቐለ 70 እንደርታው አጥቂ አማኑኤል ገ/ሚካኤል የተሻገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ቡድኑን ባለድል አድርጓል፡፡

በትናንቱ ግጥሚያ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በሁለቱም አጋማሽ የተለያየ ቡድን ይዘው በመግባት የተጫዋቾቻቸውን አቋም ገምግመዋል፡፡

ሌላኛው የወዳጅነት ግጥሚያ በመጭው ቅዳሜ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ 10፡ 00 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *