የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ጭማሪ ማሻሻያ ላደርግ ነው አለ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ጭማሪ ማሻሻያ ላደርግ ነው አለ
አርትስ 22/02/2011
አዲስ የሚተገበረው ተመን ለአራት ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን የጭማሬውን ተግባራዊነት በደንበኞች ላይ የሚደርሰውን ጫና በሚቀንስ መልኩ በአራት ተከታታይ የትግበራ ምዕራፍ ይከናወናል ተብሏል፡፡
የዋጋ ማሻሻያው ለመኖሪያ ቤት ደንበኞች እንደ ኃይል አጠቃቀማቸው በ7 እርከኖች የተከፋፈለ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
በመጀመሪያው እርከን እስከ 50 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ላለፉት 12 ዓመታት ሲያገለግል የነበረው ዋጋ በ0.2730 ሳንቲም በኪሎ ዋት ባለበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
እስከ 100 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች ወደ 0.4591 ሳንቲም በኪሎ ዋት ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡
እስከ 200 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙት ደንበኞች ደግሞ 0.7807 ሳንቲም በኪሎ ዋት ከፍ ብሏል፡፡
የዋጋ ማሻሻያው ከታህሳስ 2011 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመልክቷል፡፡
የዋጋ ማሻሻያው ያስፈለገው ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ መሆኑንም አገልግሎቱ ገልጿል፡፡