loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በኦስሎ ቀላል ግጭት ገጥሞት እንደነበረ ተነገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በኦስሎ ቀላል ግጭት ገጥሞት እንደነበረ ተነገረ

አርትስ 11/04/2011

አደጋው የደረሰው በኦስሎ አየር ማረፊያ ማክሰኞ ምሽት B787-900 በተሰኘው የአየር መንገዱ አውሮፕላን ላይ ሲሆን ፤ከመነሳቱ በፊት ክንፉ ላይ የነበረውን ግግር በረዶ እየተራገፈ በነበረበት ወቅት ከአንድ ቋሚ ፖል ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል፡፡ በግጭቱ  በአውሮፕላኑ የቀኝ ክንፍ ላይ  ቀላል ጉዳት እንዳጋጠመም ተገልጧል፡፡

አየርመንገዱ በድረ ገፁ ይፋ እንዳደረገው አደጋው ቀላል መሆኑን አስታውቆ የአውሮፕላኑ ክንፍ እስኪጠገን ሁሉም ተጓዦች ወደ ሆቴል እንዲያመሩ መደረጉን አስታውቋል፡፡

በዚህም አየርመንገዱ በተፈጠረው ክስተት ሁሉንም ተጓዦች ይቅርታ ጠይቆ፤ የታቀደውን ጉዞ አመቻችቶ መልካሙን ሁሉ ተመኝቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *